Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሚያ የግብርና ሽግግር ምክር ቤት ተመሰረተ

አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል በግብርና ዘርፍ እየተመዘገበ ያለውን ለውጥ ተቋማዊ የሚያደርግ የሽግግር ምክር ቤት ተመሰረተ።
በክልሉ ግብርናን ለማዘመንና በተቋማዊ አደረጃጀት ለመምራት አላማ ያደረገ መድረክ በአዳማ እየተካሄደ ነው።
በመድረኩ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳና የግብርና ሚኒስትር አቶ ዑመር ሁሴንን ጨምሮ የምርምር ተቋማት፣ ዩኒቨርሲቲዎችና የተለያዩ ድርጅቶች ተወካዮች ተሳትፈዋል።
በመድረኩ የክልሉ ግብርና ሽግግር ምክር ቤት በይፋ ተመስርቷል።
ምክር ቤቱ የፌዴራልና የክልሉ የግብርና ምርምር ማዕከላት፣ዩኒቨርሲቲዎችና የምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዞች፣በየደረጃው ያሉ የግብርና ሴክተሮችን በአባልነት ያቀፈ ነው ተብሏል፡፡
ክልሉን በስንዴ፣ በገብስ፣ በጤፍ፣ በጥራጥሬ፣ በቡና፣ በአትክልትና ፍራፍሬን ጨምሮ በሰባት ክላስተሮች በማደራጀት በግብርና ዘርፍ እየተዘገበ ያለውን ሽግግር ለማሳካት ምክር ቤቱ እንደተቋቋመ መገለጹን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
 
የምክር ቤቱ መቋቋም የቴክኖሎጂ አቅርቦት፣ መካናይዜሽን፤ መስኖ፣ የተሟላ የኤክስቴንሽን አገልግሎት፣ የገጠር ፋይናንስ አቅርቦት፣ገበያ ተኮር ምርቶች፣ በምግብ ራስን መቻልና ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶችን ለማሳደግ አቅም እንደሚፈጥርም ተገልጿል።
ከውጭ የሚገቡ የግብርና ምርቶችን በአገር ውስጥ መተካትና የተፈጥሮ ሀብት ልማትና አካባቢ ጥበቃ ሥራዎች በምክር ቤቱ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ሥራዎች መሆናቸውን የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱረህማን አብደላ ተናግረዋል።
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.