Fana: At a Speed of Life!

ከፍተኛ የታክስ ገንዘብ እንዲቀር በማድረግ 3 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር ጉቦ ሲቀበሉ የነበሩ የገቢዎች ሚኒስቴር ሰራተኞች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ጥር 16፣2014 (ኤፍ ቢሲ) በገቢዎች ሚኒስቴር ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቶቸ ሊፈፀሙ የነበሩ የሙስና ወንጀሎች እጅ ከፍንጅ መያዛቸውን የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው ተናገሩ፡፡
ባለፉት ወራት ሐሰተኛ ደረሰኝ ብቻ እየሸጡ የአገር ሐብት ወደ ኪሳቸው ሲያስገቡ የነበሩ 63 ድርጅቶችን ሚኒስቴሩ ማጋለጡን ያስታወሱት ሚኒስትሩ፥ በሌላ በኩል በሚኒስቴር መሥሪያ ቤታቸው ውስጥ ያሉ የውስጥ ሌቦች እንዳሉም እሙን ነው ብለዋል፡፡
በዚህም በገቢዎች ሚኒስቴር አዳማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ጉቦ ለመቀበል ተስማምተው የቅድሚያ ክፍያ 500 ሺህ ብር ሲቀበል እጅ ከፍንጅ ተይዟል ብለዋል።
በገቢዎች ሚኒስቴር ምስራቅ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት እንደዚሁ 5 ሚሊየን ብር ለመቀበል ተስማምተው የመጀመሪያ ክፍያ 200 ሺህ ብር ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል።
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ሞጆ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት 200 ሺህ ብር ሲቀበል እጅ ከፍንጅ በተመሳሳይ መያዙን፣ እንዲሁም በገቢዎች ሚኒስቴር በመካከለኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ሁለት ኦዲተሮች 12 ሚሊየን ብር ጉቦ ለመቀበል ተስማምተው የመጀመሪያ ክፍያ 100 ሺህ ብር ለመቀበል በሂደት ላይ እያሉ እጅ ከፍንጅ ለመያዝ ተችሏል ነው ያሉት።
ዛሬም ከላይ በተጠቀሱት እርምጃዎች ያልተማሩ የውስጥና የውጭ ሌቦች በተቀናጀ መንገድ የአገርና የሕዝብ ሐብት የሆነውን ከፍተኛ የታክስ ገንዘብ ለድርጅቱ እንዲቀር በማድረግ ይህን ለሚሠሩበት ውለታ 3 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር ወደ ግላቸው ሊያስገቡ ሲሉ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስታውቀዋል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.