ለአገራዊ የምክክር መድረክ ስኬት የወጣቶች ሚና ከፍተኛ ነው – ብልጽግና ፓርቲ
አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የሊጉን የስድስት ወራት የመደበኛ ስራዎች አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ውይይት እያደረገ ይገኛል፡፡
በአዳማ በአገር አቀፍ ደረጃ ያለውን የወጣቶች ሊግ የስድስት ወራት አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ በሊጉ የስራ አስፈጻሚ አባላት ውይይት እየተደረገበት መሆኑን የፓርቲው የወጣቶች ሊግ ፕሬዚዳንት አቶ አስፋው ተክሌ ገልጸዋል፡፡
አቶ አስፋው አያይዞም ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ወጣቶች በህልውና ጦርነት ወቅት ያሳዩት ተነሳሽነት ለአገራቸው ያላቸውን ፍቅርና አክብሮት ያሳየ ነበር ብለዋል።
የሊጉ አመራሮችና አባላት አውደ ውጊያ ድረስ በመሠለፍ ፣ደም በመለገስ ፣ ለመከላከያ ገንዘብ በማዋጣትና በማስተባበር፣ በማሰባሰብ ፣ የዘማች ቤተሰቦችን ሰብል በመሰብሰብ እንዲሁም የአቅመ ደካማ ሰዎችን ቤት በመገንገባት የነበረው ርብርብ የሚደነቅና በሌሎች ልማት እንቅስቃሴዎችም ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት ነው ብለዋል፡፡
የነጩ ፖስታ ለነጩ ቤተ መንግስት ንቅናቄ ከ2 ነጥብ 7 ሚሊየን በላይ ደብዳቤዎችን ወደ ነጩ ቤተ መንግስት በመላክ የኢትዮጵያን እውነታዎች ለዓለም ለማሳወቅ ንቁ ተሳትፎ ስለመደረጉ ተነስቷል።
መደረኩ ከጦርነት በኋላ የድል ማግስት መዛነፎችን በጥንቃቄ መምራትና ማስተካከል እንደሚገባም ነው የተመለከተው፡፡
ወጣቶች በአገረ መንግስት ግንባታ፣ለአካታች አገራዊ የምክክር መድረክ ውጤታማነት የበኩላቸውን ሚና መወጣት እንደሚገባቸውን ተገልጿል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!