Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለአፍሪካ ኢ-ኮሜርስ ኢንዱስትሪ የሎጀስቲክ ማዕከል ለመሆን እየሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለአፍሪካ ኢ-ኮሜርስ ኢንዱስትሪ የሎጀስቲክ ማዕከል ለመሆን እየሰራ መሆኑን አስታወቀ።
 
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም ለብሉምበርግ እንደተናገሩት፥ አየር መንገዱ የአፍሪካ የኢ-ኮሜርስ የሎጂስቲክስ ማዕከል ለመሆን የሚያስችለውን ኢንቨስትመንት በቀጣይ በጭነት እና ተያያዥ መሰረተ ልማቶች ያሳድጋል።
 
በአሁኑ ወቅት በጭነት አገልግሎት ተርሚናሉ ለኢ- ኮሜርስ የሚሆን አዲስ መጋዘን በመገንባት ላይ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።
 
ከአፍሪካ ግዙፍ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አምስት ቦይንግ 777 የጭነት ማጓጓዣ አውሮፕላኖችን ለመግዛት ዕቅድ እንዳለው፥ እንዲሁም በቀጣይም ኤርባስ ኤስ ኢ ኤ350 የተሰኘውን አውሮፕላን ሊገዛ እንደሚችልም ነው ዋና ሥራ አስፈጻሚው የገለጹት፡፡
 
በአፍሪካ እና ቻይና መካከል እየተካሄደ ያለው ኢ-ኮሜርስ እያደገ መምጣቱን የጠቀሱት ዋና ስራ አስፈፃሚው፥ በዚህ ኢንዱስትሪ ውስጥ አየር መንገዱ መሪ ሆኖ መቀጠል እንደሚፈልግ አመልክተዋል።
 
በቻይና እና አፍሪካ መካከል እየተፈፀመ ያለውን ኢ-ኮሜርስ ልውውጥ በበርካታ የአህጉሪቱ አካባቢዎች የሚገኘው ሳፋሪኮም እና የቻይናው አሊባባ ግሩብ በፈጠሩት አጋርነት በተለይም የክፍያ ስርዓቱን እያሳለጡት መሆናቸው ይነገራል።
 
ባለፉት ሁለት ዓመታት ከኮረና ቫይረስ መስፋፋት ጋር በተያያዘም በኦንላይን የሚፈፀሙ ግብይቶች መጨመራቸውንና ይህም የኢትዮጵያን ዓየር መንገድ የጭነት አገልግሎትን እንዳሳደገው አቶ ተወልደ ተናግረዋል።
 
አሁን ላይም የጭነት አገልግሎት ገቢም የአየር መንገዱን ገቢ በግማሽ እንደሚሸፍን ነው የተመለከተው።
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.