Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በድርቅ የተጎዱ አካባቢዎችን ለመጎብኘት ጅግጅጋ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በድርቅ የተጎዱ አካባቢዎችን ለመጎብኘት ጅግጅጋ ገብተዋል።
 
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጅግጂጋ ገራድ ዊልዋል አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም የክልሉ ርእሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሀመድ እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
 
በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተመራው የልዑካን ቡድን በክልሉ በድርቅ የተጎዱ አካባቢዎችን በመጎብኘት የሰብዓዊ ድጋፍ ክንውኖችን ይገመግማል።
 
በሶማሌ ክልል በተከሰተው ድርቅ ከ230 ሺህ በላይ እንስሳት ሲሞቱ፥ ከ2 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ አርብቶ አደሮች የሰብዓዊ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ከክልሉ ያገኘነው መረጃያመላክታል፡፡
 
በአልአዛር ታደለ
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.