በሰሜን ሸዋ ዞን በአጣዬ ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ5 ሰዎች ህይወት አለፈ
አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰሜን ሸዋ ዞን በአጣዬ ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ5 ሰዎች ህይወት አለፈ።
ሌሊት ከወልድያ ወደ አዲስ አበባ 22 ሰዎችን ጭኖ ሲጓዝ የነበረ ሚኒባስ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ አጣዬ ከተማ ሲደርስ በቦታው ቆሞ ከነበረ አይሱዙ የጭነት ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ ነው።
የሰሜን ሸዋ ዞን ፖሊስ መምሪያ የሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ሀላፊ ኮማንደር ተስፋዬ ግዛቸው እንደገለጹት፥ በአደጋው የ5 ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ ሲያልፍ 12 ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳትና 5 ሰዎች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል ብለዋል።
በደረሰው አደጋ በውስጡ ያሉ 6 ህጻናት ምንም ጉዳት አልደርሰባቸውም።
የአደጋው መንስኤ እየተጣራ ቢሆን፥ ምናልባትም ከአቅም በላይ መጫንና ፍጥነት ሊሆን ኮማንደር ተስፋዬ ገልፀዋል።
በአላዩ ገረመው
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!