Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ፣ ጅቡቲ እና ሩሲያ የጋራ የንግድ ፎረም አካሄዱ

አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “የኢትዮጵያ፣ የጅቡቲ እና የሩስያ ቢዝነስ ፎረም” በሚል ርዕስ በንግድ ጉዳዮች ላይ የመከረ መድረክ በሞስኮ ተካሄደ፡፡

የአፍሪካ ኢኮኖሚ ትብብር አስተባባሪ ኮሚቴ (AFROCOM) እና የሩሲያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት በመተባበር ያዘጋጁት ይህ የውይይት ፎረም በበይነ መረብ ተካሂዷል።

የኢትዮጵያ እና የጅቡቲ የንግድ ምክር ቤቶች ተወካዮች፣ ሚኒስትሮች፣ በኢትዮጵያ እና ጅቡቲ የሩሲያ ፌዴሬሽን አምባሳደሮች፣ በሩሲያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ዓለማየሁ ተገኑ እና የተለያዩ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች በፎረሙ ተሳትፈዋል።

በውይይቱ በኢትዮጵያ በኩል የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን፣ የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት እና የኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ማህበር የሥራ ኃላፊዎች ገለጻ አድርገዋል።

ፎረሙ በጥቃቅንና አነስተኛ የሩስያ የንግድ ድርጅቶች ተሞክሮ ላይ ግንዛቤ በመፍጠር ፣ የኢትዮጵያ እና የጅቡቲ የኢንቨስትመንት አቅምን በግልፅ ለማሳየት እንዲሁም የሁለትዮሽ የንግድ እና የኢኮኖሚ ግንኙነትን በማሻሻል ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ያለመ እንደሆነም ነው የተገለጸው።

ከዚህ በተጨማሪም በአፍሪካ ኢኮኖሚ ትብብር አስተባባሪ ኮሚቴ አዘጋጅነት ወደ ኢትዮጵያ እና ጅቡቲ ለሚደረጉ የንግድ ለውውጥና ትስስር እንደመነሻ እንደሚሆንም ነው የተጠቀሰው፡፡

የአፍሪካ ኢኮኖሚ ትብብር አስተባባሪ ኮሚቴ በቅርብ ጊዜ ውስጥ በሁለቱም ሀገራት የሩሲያ የንግድ ድጋፍ ማዕከላትን ለማቋቋም እየተዘጋጀ መሆኑንም ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.