የበርታ ብሔረሰብ ምክር ቤት የብሔረሰቡን መጠሪያ ሥያሜ ቤኒሻንጉል እንዲሆን ወሰነ
አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የበርታ ብሔረሰብ ምክር ቤት የብሔረሰቡ መጠሪያ ሥያሜ ቤኒሻንጉል እንዲሆን ወሰነ፡፡
የበርታ ብሔረሰብ ምክር ቤት 8ኛ መደበኛ ጉበዔውን በኩርሙክ ወረዳ እያካሄደ ይገኛል፡፡
ጉባዔው በኩርሙክ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ እስማኢል አብዱራሀማን የእንኳን ደህና መጣቹ መልዕክትና በሃይማኖት አባት ጸሎት ተጀምሯል፡፡
ሥያሜውን ለመቀየር የተጠናዉ ጥናት በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡
በጥናቱ ሰፊ ዉይይት ያደረገዉ ምክር ቤቱ የብሔረሰቡን መጠሪያ ሥያሜ ቤኒሻንጉል እንዲሆን ወስኗል ነው የተባለው፡፡
የብሔረሰቡ ምክር ቤት ከተመሰረተበት ከ2006 ዓ.ም ጀምሮ በርካታ ሥራዎችን ሲሰራ መቆየቱ የተጠቆመ ሲሆን በተለይ የብሔረሰቡን ባሕል፣ ታሪክና ትውፊት ለቀጣይ ትውልድ ለማስተላለፍ የሚያስችሉ ሥራዎች እየተሰሩ ነውም ተብሏል፡፡
በጉበዔው የባለፈዉ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርትና በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡
በጉባዔው የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር እና የብሔረሰቡ ምክር ቤት አባል አቶ አሻድሊ ሀሰን መገኘታቸውን የቤንሻንጉል ጉሙዝ መገናኛ ብዙኃን መረጃ አመላክቷል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!