Fana: At a Speed of Life!

ዶክተር ይልቃል ከፋለ የአጅማ ጫጫ መስኖ ልማት ፕሮጀክት ግድብ ግንባታን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ዶክተር ይልቃል ከፋለ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን እየተገነባ ያለውን የአጅማ ጫጫ መስኖ ልማት ፕሮጀክት ግድብ ግንባታን ጎበኙ፡፡
በጉብኝቱ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ ሥምሪትና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ደኤታ ንጉሡ ጥላሁን እንዲሁም ሌሎች የክልል አመራሮችና እና የሥራ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል፡፡
የመስኖ ልማት ፕሮጀክቱ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን አንጎለላ ጠራ ወረዳ የሚገነባ ሲሆን፥ ባለፈው ዓመት ነው ግንባታው በይፋ የተጀመረው፡፡
ግድቡ 45 ነጥብ 5 ሜትር ከፍታ እና 371 ሜትር ርዝመት ሲኖረው፥ 55 ሚሊየን ሜትር ኪዩብ ውሃ የመያዝ አቅም እንዳለው ተገልጿል።
በ5 ቢሊየን ብር በጀት የሚገነባው ፕሮጀክት ግንባታ በሦስት ዓመታት ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሏል፡፡
ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅም 7 ሺህ ሄክታር በማልማት ከ28 ሺህ በላይ አባወራዎችንና እማወራዎችን ተጠቃሚ ያደርጋል ነው የተባለው።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.