Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያውያን በአንድነት ሆነው የጀመሩትን ዲፕሎማሲያዊ ትግል ማጠናከር አለባቸው – የአሜሪካ ሴናተሮች

አዲስ አበባ፣ ጥር 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አሜሪካውያን የዜጎች ምክር ቤት ከናቫዳ ግዛት የምክር ቤት አባል (ስናተር) ካትሪን ማሳቶ እና የኮሎራዶ ግዛት የምክር ቤት አባል ጀይሰን ክሮው ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ተወያዩ።

ሴናተር ካትሪን ማሳቶ በውይይታቸው ፥ የኢትዮጵያን ጉዳይ በትኩረት እየተከታተሉ መሆናቸውን ለምክር ቤቱ ተወካዮች አስረድተዋል፡፡

ኢትዮጵያ እና አሜሪካ ለረዥም ጊዜ የዘለቀ መልካም ግንኙነት እንዳላቸው አንስተው ፥ ይህንን ግንኙነት በቀላሉ የምናፈርሰው አይደለም ሲሉ ነው የገለጹት።

በመሆኑም ጉዳዩን በጥልቀት ለመከታተል ዝግጁ መሆናቸውን በማረጋገጥ ፥ ኢትዮጵያውያን በአንድነት ሆነው የጀመሩትን የዲፕሎማሲ ጥረት መግፋት እንዳለባቸው መክረዋል።

በተያየዘ ኮንግረስማን ጀይሰ ክሮው የጆ ባይደን አስተዳደር አጎዋን በመጠቀም ህወሓትን ለመደገፍ የወሰደው እርምጃ የኢትዮጵያን ህዝብ የሚጎዳ እንደሆነ ነው የጠቆሙት፡፡

ለሰብዓዊ እርዳታ ተብለው የተዘረጉ ፕሮጀክቶችን ለፖለቲካዊ ጥቅም ማዋል አሜሪካዊ ባህሪ አይደለም ሲሉም ለምክር ቤቱ ተወካዮች ገልጸውላቸዋል፡፡

ሴናተር ጀይሰን ክሮው አክለውም ፥ የአጎዋን ጉዳይ እንደሚያውቁና ጉዳዩን በቅርበት እንደሚከታተሉት መግለጻቸውን ከኢትዮጵያ አሜሪካውያን የዜጎች ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.