Fana: At a Speed of Life!

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽንን አሰራሮች ማሻሻል ያለመ ጉብኝት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥር 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ያለበትን ወቅታዊ ሁኔታ ለመረዳትና አሰራሮችን ለማሻሻል ያለመ ጉብኝት ተካሄደ፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር በለጠ ሞላ እና የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሳንዶካን ደበበ የአይሲቲ ፓርክን የስራ እንቅስቃሴ ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝቱ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ባይሳ በዳዳ፣ የአይሲቲ ፓርክ ስራ አስኪያጅን እንዲሁም ሌሎች የፓርኩ የሥራ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል፡፡

የአይሲቲ ፓርክ ስራ አስኪጅ አቶ ሱራፌል ሽመልስ÷ ፓርኩ ለኢትዮጵያ እያበረከተ ያለውን አስተዋጽኦ፣ ያለበትን ወቅታዊ የሥራ ሁኔታ ከመሰረተ ልማት ግንባታ፣ ከኃይል ማሻሻያ እንዲሁም በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ጉብኝቱ ፓርኩ ያለበትን ወቅታዊ ሁኔታ ለመረዳትና በሚያጋጥሙ ችግሮች ዙሪያ እንዲሁም መሻሻል ባለባቸው አሰራሮች ላይ አብሮ ለመስራት ጠቃሚ መሆኑን ዶክተር በለጠ ተናግረዋል፡፡

በቀጣይም በዘርፉ በቅንጅት መስራት የሚቻልባቸውን አማራጮች መጠቀም እንደሚገባ መግለጻቸውንም ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.