Fana: At a Speed of Life!

የትምህርት ሚኒስቴር የስዊዲን መንግስት የወደሙ ትምህርት ቤቶችን በመገንባቱ ሂደት እገዛ እንዲያደርግ ጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የስዊዲን መንግስት የወደሙ ትምህርት ቤቶችን በመገንባቱ ሂደት እገዛ እንዲያደርግ ጥሪ አቀረቡ፡፡
 
ሚንስትሩ በኢትዮጵያ የስዊዲን አምባሳደር ሃንስ ሄንሪክ ጋር በወደሙ ትምህርት ቤቶች ግንባታ ዙሪያ ውይይት ባደረጉበት ወቅት ነው ጥሪውን ያቀረቡት፡፡
የትምህርት ሚኒስትሩ የስዊዲን መንግስት ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ በርካታ ጥራት ያላቸው ትምህርት ቤቶችን ገንብቶ አገልግሎት እየሰጡ መሆናቸውን አስታውሰው በአሁኑ ወቅት በአሸባሪው የህውሃት ቡድን የወደሙ ትምህርት ቤቶችን ደረጃቸውን በጠበቀ ሁኔታ መልሶ ለመገንባት መንግስት እያደረገ ያለውን ጥረት ለማገዝ ትኩረት እንዲሰጥ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡
 
የስዊዲን አምባሳደር ሃንስ ሄንሪክ በበኩላቸው አገራቸው የትምህርት ተቋማትን በጥራት መልሶ ከመገንባት አንፃር ወደፊት ምላሽ እንደምትሰጥ መግለጻቸውን ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

በተመሳሳይ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በኢትዮጵያ ከሀንጋሪ አምባሳደር አቲላ ቶማስ ጋር በነፃ የትምህርት ዕድል ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡

ሚኒስትሩ ከዚህ ቀደም የሀንጋሪ መንግስት ለኢትዮጵያውያን ይሰጥ የነበረውን የነፃ የትምህርት ዕድል ስምምነት በማስቀጠል የሁለቱን አገራት ወዳጅነት ማጠናከር እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

 

አምባሳደር አቲላ ቶማስ በበኩላቸው÷ አገራቸው በሁለተኛ ዲግሪ እና በሶስተኛ ዲግሪ ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን ነፃ የትምህርት ዕድል ከዚህ ቀደሙ በተሻለ ሁኔታ ቁጥሩን በመጨመር እንደምትሰጥ አረጋግጠዋል፡፡

የነፃ የትምህርት እድሉ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት እንደሚያጠናክርም በውይይቱ ተነስቷል።

 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.