ወደ ትግራይ የሚገባውን የሰብዓዊ ድጋፍ ህወሓት ሙሉ በሙሉ አግዷል – አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ
አዲስ አበባ፣ ጥር19፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) አሸባሪው የህወሓት ቡድን በቅርብ ጊዜ በአፋር ክልል በከፈተው ጥቃት ከ200 ሺህ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸውን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ ሙሉ መልዕክተኛ አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ገለጹ፡፡
አሸባሪው የህወሓት ቡድን አሰቃቂ ጥቃት የፈጸመባቸው የአፋር አካባቢዎችም ፥ አባላና ማጋሌ ከተሞች እንዲሁም ባራህሌ እና ኢሬብቲ መሆናቸውን አምባሳደሩ ጠቁመዋል፡፡
አምባሳደሩ አክለውም ፥ አሸባሪው የህወሓት ቡድን የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት ለአካባቢው ነዋሪዎች ለማድረስ የሚደረገውን ጥረት አስቸጋሪ እንዳደረገውና አዲስ ጥቃት በመክፈት በየብስ ይደርስ የነበረውን የሰብዓዊ እርዳታን ሙሉ በሙሉ ማገዱን ነው አምባሳደሩ ለተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ያስረዱት።
አሸባሪው ቡድን ጥቃቶቹን አቅዶ እንደፈጸመና በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ተጨማሪ መፈናቀል እና ስቃይ ለማድረስ እየሰራ መሆኑን አምባሳደሩ አብራርተዋል።