Fana: At a Speed of Life!

በአቶ አህመድ ሺዴ የተመራው ልኡክ ከሳውዲ ባለስልጣናት ጋር በሁለቱ ሀገራት የጋራ ሰብአዊና የእርዳታ ጉዳዮች ላይ ተወያየ

አዲስ አበባ፣ ጥር 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ የተመራው የኢትዮጵያ የልኡካን ቡድን ከሳውዲ አረቢያ የንጉስ ሰልማን የሰብአዊ እርዳታ ማእከል የበላይ ሀላፊ ከዶ/ር አብዱላህ አልራቢሀ ጋር በሁለቱ ሀገራት የጋራ ሰብአዊና የእርዳታ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ፥ ከሳውዲ ልማት ፈንድ ስራ አስኪያጅ ሱልጣን አልማርሻድ ጋርም ተገናኝተው የተወያዩ ሲሆን፥ በሳውዲ ልማት ፈንድ የገንዘብ ድጋፍ በኢትዮጵያ የሚያካሄዱትን የልማት ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶች ያሉበትን ሁኔታ በጋራ ገምግመዋል፡፡

በሳውዲ ልማት ፈንድ የገንዘብ ድጋፍ በኢትዮጵያ የሚካሄዱ የልማት ፕሮጀክቶችና ፕሮግራሞች በመሰረተ ልማት አውታሮች ዝርጋታና ዘላቂ ልማትን ለማምጣት በሚደረገው ጥረት በሀገሪቱ ማህበራዊ አገልግሎትና በኢኮኖሚ እድገት ላይ አዎንታ አስተዋጾኦ እንዳላቸው አመልከተዋል፡፡

ሳውዲ አረቢያ በሰብአዊ እርዳታና በኢኮኖሚ ልማት ለምታደርገው አስሰተዋጽኦ አድናቆታቸውን መግለፃቸውን ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.