Fana: At a Speed of Life!

ወልድያ፣መርሳ፣ ውጫሌ እና በአካባቢያቸው ባሉ ከተሞች የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጡ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ጥር 20፣2014 (ኤፍ ቢሲ) በ66 ኪሎ ቮልት ኤሌክትሪክ አስተላላፊ መስመር ተሸካሚ ምሰሶ ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ ወልድያ፣ መርሳ፣ ውጫሌ እና በአካባቢያቸው ባሉ ከተሞች የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጡን የአማራ ክልል ኤሌክትሪክ  አገልግሎት አስታውቋል፡፡

ከደሴ ማከፋፈያ ጣቢያ እስከ ወልድያ ማከፋፋያ ጣቢያ በተዘረጋው 66 ኪሎ ቮልት የኤሌክትሪክ አስተላላፊ መስመር ላይ ሀብሩ ወረዳ ቀርጨም በር ቀበሌ አካባቢ በባለ አራት ቋሚ ምሰሶ ላይ ባልታወቀ ምክንያት በደረሰ የእሳት አደጋ ምሶሶዎቹ ሙሉ በሙሉ በመቃጠላቸው ወልድያ፣ መርሳ፣ውጫሌ እና በአካባቢያቸው ባሉ ከተሞች የኤሌክትሪክ ኃይል ተቋርጦባቸዋል፡፡

ምሶሶዎችን በመተካት አገልግሎቱን ወደ ነበረበት ለመመለስ ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን የገለፀው አገልግሎቱ፥ ህዝቡ በትእግስት እንዲጠብቅ ጠይቋል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.