አንድ ስናይፐር ጠብመንጃ ፣ ከ20 ሺህ በላይ የክላሽና 260 የብሬን ጥይት ከእነ ተጠርጣሪዎቹ ተያዘ
አዲስ አበባ፣ ጥር 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ፖሊስ እና የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት በጋራ በመቀናጀት ባደረጉት ኦፕሬሽን አንድ ስናይፐር ጠብመንጃ ፣ ከ20 ሺህ በላይ የክላሽ እና 260 የብሬን ጥይት ከእነ ተጠርጣሪዎቹ መያዛቸውን አስታወቁ፡፡
ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውርን ለመቆጣጠር እየተሰራ ያለው ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉን ፖሊስ አስታውቋል፡፡
በኤፍ .ኤስ አር አይሱዙ የጭነት ተሽከርካሪ አካል ላይ መሸሸጊያ በማሰራት ከወሊሶ ወደ አዲስ አበባ ሲጓጓዝ የነበረ አንድ ስናይፐር ጠብመንጃ፣ 20 ሺህ 630 የክላሽን -ኮቭ ጠብመንጃ እና 260 የብሬን ጥይት ጥር 20 ቀን 2014 ዓ.ም በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ልዩ ቦታው እህል በረንዳ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት እና የአዲስ አበባ ፖሊስ በመተባበር ባከናወኑት ኦፕሬሽን በቁጥጥር ስር እንዳዋሉ ተገልጿል፡፡
ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያዎቹን ሲያዘዋውሩ የተገኙ የመኪናው ሾፌርና የጦር መሳሪያውን ያስጫነው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራው መቀጠሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጨምሮ ገልጿል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!