Fana: At a Speed of Life!

በወልድያ ከተማና አካባቢያው ተቋርጦ የነበረው የኤሌክትሪክ ኃይል ዳግም አገልግሎት መስጠት ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥር 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ ምሰሶዎች ላይ በደረሰ ቃጠሎ የተነሳ በወልድያ ከተማና አካባቢያው ተቋርጦ የነበረው የኤሌክትሪክ ኃይል ዳግም አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።
ትናንት የደረሰውን የኤሌክትሪክ ምሰሶ ቃጠሎ በሌላ በመተካት ወልድያ፣መርሳ፣ ውጫሌ እና አካባቢያቸ ዳግም ኤሌክትሪክ እንዲያገኙ ርብርብ ሲደረግ ቆይቶ ወልድያ ከተማ ከደቂቃዎች በፊት ኤሌክትሪክ ማግኘት ችላለች።
 
በየደረጃውም ሌሎች ከተሞች ኤሌክትሪክ እንደሚያገኙ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የማስተላለፊያ መስመሮች የቴክኒክ ድጋፍ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ መንግስቴ መግለፃቸውን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይለር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.