Fana: At a Speed of Life!

የእናቶችን ሞት ማስቀረት ሁለንተናዊ ማህበራዊ ችግርን መፍታት ማለት ነው – ዶክተር ደረጀ ዱጉማ

አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 16ኛው ሀገር አቀፍ የጤናማ እናቶች ወር “ከወሊድ በኋላ በደም መፍሰስ ምክንያት የሚከሰተውን የእናቶች ሞት እጅ ለእጅ ተያይዘን እንግታ “ በሚል መሪ ቃል በደሴ ከተማ ተከበረ፡፡

በመርሀ ግብሩ ላይ የተገኙት የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ ዱጉማ፥ የእናቶችን ሞት ማስቀረት ሀገራዊ ሁለንተናዊ ማህበራዊ ችግርን መፍታት ማለት ነው ብለዋል፡፡

ጤናማ እናትን ለመፍጠር የመንግስት ጤና ተቋማት፥ አመራሮችና ባለሙያዎች ጥረት ብቻ ሳይሆን የመላው የአጋር አካላትና የማህበረሰቡ ትብብር ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት በሀገራችን በዓመት ከ11 ሺህ በላይ እናቶች በእርግዝናና በወሊድ ምክንያት እንደሚሞቱና ይህም በቀን ከ30 በላይ እናቶች ለሞት ይዳረጋሉ ነው ያሉት፡፡ ይህም አሳሳቢ መሆኑን ነው የገለጹት።

ይህንን ሀገራዊ ችግር ለመፍታት እስከአሁን ከተሠሩት ተግባራት በላቀ ደረጃ ለመስራት የ አቅምን አጠናክረን እንሰራለን ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው።

የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ሀላፊ ዶ/ር ጋሹ ክንዱ በበኩላቸው፥መ በክልሉ የእናቶች ሞትን ለማስቀረት ከቀበሌ ጤና ኤክስቴንሽን እስከ ሆስፒታል ድረስ ከዚህ ቀደም ከነበረው የተሻለ ስራ እየተከናወነ ነው ብለዋል።

የነበሩት ስኬቶችን አጠናክሮ በመቀጠል በሽብር ቡድኑ ወረራ ምክንያት ከፍተኛ ውድመት ለደረሰባቸው አካባቢዎች ልዩ ትኩረት እንደሚሰጥም ገልጸዋል።

በአለባቸው አባተ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.