ፕሬዚደንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ለ35 ችግረኛ እናቶች የሥራ ማስጀመሪያ የገንዘብ ድጋፍ አደረጉ
አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኤፌዴሪ ፕሬዚደንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በሚኖሩበት በአራዳ ክፍለ ከተማ በአስከፊ ህይወት ውስጥ ለነበሩ 35 እናቶች የስራ ማስጀመሪያ ድጋፍ ማድረጋቸውን የፕሬዚደንት ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡
ፕሬዚደንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በሚኖሩበት በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 በአስከፊ የኑሮ ሁኔታ ውስጥ ለሚገኙ ሴቶች የኢኮኖሚ ድጋፍ ሲሰጡ መቆየታቸውን ጽህፈት ቤቱ ገልጿል።
የአካባቢው በርካታ እናቶች ደቃቅ ከሰል ከአፈር በመደባለቅ በድጋሚ አገልግሎት በማዋል እና በሌሎች እጅግ ዝቅተኛ ገቢ በሚያስገኙና ለጤና ጠንቅ በሆኑ ሥራዎች የተሰማሩ መሆናቸው ተጠቁሟል።
በመሆኑም ሴቶቹ ሥራቸውን መቀየር የሚያስችል የመሠረታዊ የንግድ ክህሎት ሥልጠና እንደተሰጣቸው እና በዛሬው ዕለትም ለ35 እናቶች ሥራ ማስጀመሪያ ገንዘብ ድጋፍ ማግኘታቸው ተነግሯል።
ከእነዚህም መካከል የወረዳው አስተዳደር ለ12 ሴቶች የመሥሪያ ቦታ አመቻችቷል።
ከዚህ ቀደም 50 የሚሆኑ ሴቶች ተመሳሳይ ድጋፍ ማግኘታቸውን ጽህፈት ቤቱ ጭምሮ ገልጿል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!