Fana: At a Speed of Life!

ተቋሙ በአፋር ክልል ለተፈናቀሉ ወገኖች የ5 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አሸባሪው ህወሓት በአፋር ክልል በፈፀመው ወረራ ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚውል የ5 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የዓይነትና የገንዘብ ድጋፍ አደረገ።

ድጋፉን ለክልሉ የፋይናንስና ኢኮኖሚ ቢሮ ኃላፊና የሀብት አሰባሳቢ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አህመድ መሐመድ ዛሬ ያስረከቡት የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሙላት ገዛኸኝ ናቸው።

በርክክብ ሥነ ስርዓቱ ላይ አቶ ሙላት ገዛኸኝ እንደገለፁት ፥ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በጦርነቱ የወደሙ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶችን ከመጠገን ጎን ለጎነ የተቋሙ አመራርና ሠራተኞች በጦርነቱ የተፈናቀሉ ወገኖችን ለመርዳት 2 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ግምት ያለው የዓይነት እንዲሁም 3 ሚሊየን ብር የጥሬ ገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል።

ተቋሙ ሠራተኞቹን በማስተባበር ያደረገው የዓይነት ድጋፍ፥ የህፃናት አልሚ ምግብ፣ መኮረኒ፣ ዱቄት፣ አልባሳትና የንጽህና መጠበቂያ ቁሶችን ያካተተ ነው።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከፍተኛ የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማቶችን በፍጥነት በመጠገን ከአፋር ህዝብ ጎን መቆሙን በተግባር በማሳየቱ አመስግነዋል።

በአሁኑ ወቅት በህወሓት ጦርነት የተከፈተባቸውና የተወረሩ አካባቢዎች ነፃ ሲወጡ እንደ ከዚህ ቀደሙ ድጋፉ እንደማይለየን እምነት አለን ሲሉ ተስፋቸውን ገልፀዋል።

በክልሉ በዞን ሁለት አምስት ወረዳዎች ብቻ ከ300 ሺህ ሰዎች በላይ ተፈናቅለው እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ነው ኃላፊው ያመለከቱት።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ቀደም ሲል በአማራ ክልል በጦርነቱ ለተፈናቀሉ ወገኖች 7 ሚሊየን ብር የዓይነትና የገንዘብ ድጋፍ ማድረጉን ከኤሌክትሪክ ኃይል ያገኘነው መረጃ አስታውሷል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.