የአውሮፓ ህብረት አባል አገራት ለኢትዮጵያ 13 ሚሊየን ዶዝ የኮቪድ-19 ክትባት ለገሱ
አዲስ አበባ፣ ጥር 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ህብረት አባል አገራት ለኢትዮጵያ 13 ሚሊየን ዶዝ የኮቪድ-19 ክትባት ለገሱ።
ድጋፍ ካደረጉ የአባል አገራቱ መካከልም ፈረንሳይ፣ ፊንላንድ፣ ዴንማርክ፣ ግሪክ፣ ጣልያን እና ስዊድን ይገኙበታል፡፡
ድጋፉም የጤና ሚኒስቴር በመላው ኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ክትባት ስርጭት ለማዳረስ የሚያደርገውን ጥረት እንደሚያግዝ ተገልጿል፡፡
ከዚህ ቀደም የተለያዩ የአውሮፓ አባል አገራት ከ24 ሚሊየን ዶዝ በላይ የኮቪድ-19 ክትባት ለኢትዮጵያ መለገሳቸውን በኢትዮጵያ ከሚገኘው የፈረንሳይ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!