የአንጋፋው ሀገር ፍቅር ቴአትር ዕድሳት ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ፣ ጥር 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ የሚገኘው የአንጋፋው ሀገር ፍቅር ቴአትር ዕድሳት ስራ መጠናቀቁ ተገለጸ፡፡
በ1927 ዓ.ም ሀገርን ከጠላት ወረራ ለመታደግ ይቻል ዘንድ ሀገር ፍቅር ማህበር ተብሎ የተመሰረተውና ቀጥሎ በ1960 ዓ.ም ሀገር ፍቅር ቴአትር ተብሎ የተቋቋመው አንጋፋው ቴአትር ቤት ታሪካዊ ይዘቱንና የምህንድስና ጥበቡን ሳይለቅ ዘመኑን እና የቴአትር ቤቱን ስም በሚመጥን መልኩ ዕድሳቱ ተጠናቆ የመጀመሪያ ርክክብ ተደርጓል፡፡
ላለፉት 20 ዓመታት አንዳችም ዕድሳት ያልተደረገለት ቴአትር ቤቱ የዕድሳት ስራው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተከናውኖ በዛሬው ዕለት ርክክብ መደረጉን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
610 መቀመጫዎች አሉት የተባለውን ዋናውን የቴአትር ማሳያ አዳራሽ ጨምሮ አርት ጋለሪ፣አነስተኛ የቴአትር አዳራሽ፣ ዘመናዊ የሙዚቃ መከወኛ ክፍል፣ ካፊቴሪያ፣ አስተዳደር ህንፃ እና ሌሎችም አገልግሎቶች የተካተቱበት መሆኑ ተገልጿል፡፡
ቴአትር ቤቱ ለተደራሲው ከፍ ያለ ምቾትን ከማጎናፀፉም በተጨማሪ የጥበብ ሰዎችንም ለተሻለ የፈጠራ ስራ የሚያነሳሳ ምቹ እና ፅዱ የኪነጥበብ ቤት ሆኖ የዕድሳት ስራው ተጠናቋል ነው የተባለው፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!