Fana: At a Speed of Life!

የሶማሌ ክልል “መመረጥ ተለውጦ ሀገርን ለመለወጥ” በሚል መሪ ቃል የውይይት መድረክ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥር 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ብልፅግና ፓርቲ “መመረጥ ተለውጦ ሀገርን ለመለወጥ” በሚል መሪ ሀሳብ የአመራር ግንባታ የውይይት መድረክ በጅግጅጋ ከተማ ማካሄድ ጀመረ፡፡

በመድረኩ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሀመድን ጨምሮ የክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ኡስማን እና የሶማሌ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሃላፊ ኢንጅነር መሀመድ ሻሌ ተገኝተዋል።

ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎችም በተገኙበት ለመድረኩ በተዘጋጀው ሰነድ ዙሪያ ውይይት ተደርጓል፡፡

ሀገራዊውና የክልሉ የፖለቲካና የአስተዳደር ታሪክ የራሱን ቀለምና ቅርጽ ይዘት በሚመለከት የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሙስጠፌ መሀመድ ገለጻ አድርገዋል፡፡

አሁን በተጀመረው የአመራር ግንባታ አካሄድ ፓርቲው ብቁ አመራር እየገነባ የጠራ እሳቤ ይዞ እንደሚወጣም ተናግረዋል።

ብልፅግና በምርጫ ያገኘው ድልን ሳይሆን ህዝብ የማገልገል ዕድልን ጭምር ነው ያሉት ደግሞ የሶማሌ ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ኢንጅነር መሀመድ ሻሌ ናቸው፡፡

ይህን ሃላፊነት ለመወጣት የአገልጋይነት መንፈስ ተላብሶ አገራዊ ሃላፊነትን በአግባቡ የሚወጣ አመራር ማብቃት ያስፈልጋልም ብለዋል።

የአመራር፣ የተግባር ጥንካሬና የፓርቲ ስነ ምግባርን ከፍ በማድረግ የእያንዳንዱ አመራር ጥንካሬ እየጎለበተ፥ ድክመቱ የሚታረምበት መድረክ እንደሆነ ማስረዳታቸውንም ከክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.