መሀል ሜዳ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አገልግሎት መሥጠት ጀመረ
አዲስ አበባ፣ ጥር 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሸባሪውና ዘራፊው የህወሓት ቡድን ጉዳት ደርሶበት የሕክምና አገልግሎት ያቋረጠው የመሀል ሜዳ ሆስፒታል በተደረገለት ድጋፍ አገልግሎት መሥጠት ጀመረ፡፡
የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታሉ ÷በዳግማዊ ምኒልክ ሆስፒታልና በአካባቢው ማኅበረሰብ በተደረገለት ድጋፍ የሕክምና አገልግሎት መሥጠት መጀመሩን የሆስፒታሉ ሥራ አስኪያጅ ወርቅነህ ዘዉዴ ተናግረዋል።
ሥራ አስኪያጁ ÷ሆስፒታሉ በተደረገለት የሕክምና መገልገያ መሳሪያዎችና የመድኃኒት አቅርቦት ድጋፍ የእናቶችና የሕፃናት ጤና አገልግሎት፣ የድንገተኛና ጽኑ ሕሙማን አገልግሎት እንዲሁም የተመላላሽ ሕክምና አገልግሎቶችን መሥጠት ጀምሯል፡፡
በየዕለቱ በአማካይ ከ 150 እስከ 200 ታካሚዎች አገልግሎት እያገኙ እንደሚገኝም ነው የተመለከተው፡፡
ሆስፒታሉ በሙሉ አቅሙ እንዲሠራ ተጨማሪ ድጋፎች እንደሚያስፈልጉም ሥራ አስኪያጁ ተናግረዋል።
በመሀል ሜዳ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የሚሠሩ የህክምና ባለሙያዎች ÷ የአምቡላንስ አገልግሎት በመስተጓጎሉ በእናቶችና በድንገተኛ ጤና አገልግሎት ላይ ተጽእኖ ማሳደሩን መግለጻቸውን የጤና ሚኒስቴር በመረጃው አመላክቷል::
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን