Fana: At a Speed of Life!

ባንኩ ያለካርድ ከኤቲኤም ማሽን ገንዘብ ማውጣት የሚያስችል አገልግሎት መስጠት ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥር 23 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያለካርድ ከኤቲኤም ማሽን ገንዘብ ማውጣት የሚያስችል አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አስታወቀ፡፡

ደንበኞች ከሲቢኢ ብር ሒሳባቸው ያለካርድ ከኤቲኤም ማሽን ገንዘብ ማውጣት የሚችሉበትን አሠራር ባንኩ ተግባራዊ ማድረጉ ተገልጿል፡፡

በዚህ አገልግሎት ደንበኞች ከራሳቸው በተጨማሪ ለሚፈልጉት ሌላ ግለሰብ ያለካርድ በኤቲኤም ማሽን አማካይነት ከሲቢኢ ብር ሒሳባቸው ገንዘብ እንዲያወጣ ማድረግ ይችላሉም ነው የተባለው፡፡

የአገልግሎቱን አጠቃቀም መመሪያ ከተቋሙ የድረ-ገጽ አድራሻ መመልከት እንደሚቻል ከባንኩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.