Fana: At a Speed of Life!

በአፋር ክልል የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ያልወሰዱ ተማሪዎች ፈተና እየወሰዱ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፋር ክልል በተለያዩ አካባቢዎች አሸባሪው ህወሓት በፈፀመው ወረራ ምክንያት የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ያልወሰዱ ተማሪዎች ዛሬ ፈተና መውሰድ ጀምረዋል፡፡
የአፋር ክልል ትምህርት ቢሮ የመማር ማስተማር ዳይሬክተር አቶ ወልዱ ሀይሰማ በክልሉ ፈተና ያልወሰዱ ተማሪዎች በሁለተኛ ዙር ፈተና እየወሰዱ እንደሚገኙ ተናግረዋል።
በሁለተኛው ዙር ብሔራዊ ፈተና ለመውሰድ 257 ተማሪዎች የተመዘገቡ ሲሆን፥ ከዚህ ውስጥ 154 ተማሪዎች ተገኝተው ፈተናውን መውሰድ ጀምረዋል።
ለ3 ተከታታይ ቀናት የሚቆየው ፈተና በሰመራ ከተማ ማዕከል በሚገው የሰመራ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እየተሰጠ ይገኛል።
አሁንም ጁንታው ወረራ የፈፀመ እና በንፁሀን ዜጎች ላይ ጉዳት እያደረሰ ይገኛል ያሉት ዳይሬክተሩ፥ በዚህ ምክንያት በሁለተኛው ዙር ፈተና ላልተገኙ በቀጣይ እንዲሚፈተኑ ተናግረዋል።
ተማሪዎች የሰነ-ልቦና ችግር እንዳይገጥማቸው ከአጋሮች ጋር በመተባበር የስነ -ልቦና ትምህርት ይሰጣል ሲሉ ዳይሬክተሩ አቶ ወልዱ ሀይሰማ ገልፀዋል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.