Fana: At a Speed of Life!

ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ለተፈናቃዮች ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ከወለጋ፣ አምቦ ባኮትቤ ወረዳ እና ከሌሎችም የኦሮሚያ ክልል ወረዳዎች በሸኔ የሽብር ቡድን ተፈናቅለው በደብረብርሃን ከተማ ለሚገኙ ከ6 ሺህ በላይ ተፈናቃዮች የምግብ፣ የአልባሳትና የንጽህና መጠበቂያ ድጋፍ አደረገ፡፡
የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ የቤተመጻህፍትና ዶክመንቴሽን ቡድን መሪና የድጋፉ አስተባባሪ ይድነቃቸው ፈለቀ እንዳሉት÷ የዩኒቨርሲቲው ማኔጅመንት በወሰነው መሰረት ከ4 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የምግብ፣ ፍራሽና የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን ለተፈናቃዮች ድጋፍ ተደርጓል፡፡
የተፈናቃዩ ቁጥር በየቀኑ እየጨመረ በመሆኑ የቦታ እጥረትና መጨናነቅ ስላለ ለኮቪድና ለሌሎች ተላላፊ በሽታዎች ጭምር ስለሚያጋለጥ ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡
ድጋፍ የተደረገላቸው ተፈናቃዮች በበኩላቸው÷ የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ በምግብና አልባሳት በኩል ላደረገላቸው ድጋፍ አመስግነው÷ ተገደው ቀያቸውን እንዲለቁ መደረጋቸውን ተናግረዋል፡፡
መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍና እርዳታ እንዲያደርግላቸው እና የመልሶ እንዲያቋቁማቸው መጠየቃቸውን ከደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.