የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ6ኛ ዙር ተመራጭ ሴቶች ኮከስ የምስረታ ጉባኤ ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ6ኛ ዙር ተመራጭ ሴቶች ኮከስ የምስረታ ጉባኤ ተካሄዷል፡፡
ኮከሱ በየአምስት አመቱ አዲስ ምክር ቤት ሲቋቋም አብሮ የሚመሰረት ሲሆን፥ አላማውም የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎ፣ መብትና ጥቅም ማስከበር ነው ተብሏል፡፡
በፖለቲካ ሥልጣን ክፍፍል የሴቶችን ተሳትፎ ፍትሃዊነት እንዲኖረው ከማድረግ አንፃር ሰፊ ስራ መሰራቱን በጉባኤው በቀረበው ሰነድ ተገልጿል፡፡
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ ሎሚ በዶ፥ የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሣትፎና ተጠቃሚነትን በተሟላ እና ውጤታማ በሆነ መልኩ ለማረጋገጥ ኮከሱ ጠንክሮ እንዲሰራ ነው ያሳሰቡት፡፡
በምስረታ ጉባኤው የሴቶች ኮከስ የ5 ዓመት ስትራቴጂክ እቅድ እና የ2014 በጀት ዓመት እቅድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበት በሙሉ ድምጽ ፀድቋል መባሉን ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!