የድሬዳዋ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ የአመራር ግንባታ መድረክ ማካሄድ ጀመረ
አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ አመራሮች የአቅም ግንባታ ውይይት ማካሄድ ጀመሩ።
በአመራሮች የአቅም ግንባታ የውይይት መድረክ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሀርን ጨምሮ ሌሎች የሥራ ሃላፊዎች ተሳትፈዋል፡፡
ከድህረ ጦርነት በኋላ የተገኙ ድሎችን በአግባቡ ለማስቀጠል ሁሉም አመራር ወቅቱ በሚፈልገው አቋም ላይ መገኘት እንደሚገባው የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ተናግረዋል፡፡
መድረኩ ፓርቲው ለህዝብ የገባውን ቃል በተግባር ለመመለስ፣ በአገልጋይነት መንፈስ የህዝብን ጥያቄ ምላሽ እንዲያገኝ ለማድረግ እና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት ያለመ መሆኑን የገለጹት ደግሞ የድሬዳዋ ብልፅግና ፓርቲ ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ ናቸው፡፡
በቀጣይ የጎራ መደበላለቅ ውስጥ የሚገኙ አመራሮችን አቅም በመገንባት የሚቀጥሉትን በማስቀጠል፣ የሚታረሙትን በማረምና የሚቆረጡትን በማሰናበት አስተዳደራዊ የልማት አጀንዳን በአግባቡ መወጣት እንደሚያስፈልግም ተመላክቷል።
በመድረኩ ላይ የአገልጋይነት መንፈስን ተላብሶ አገራዊ ሃላፊነትን የሚወጣ አመራር ማልማትና ማብዛት ያስፈልጋልም ነው የተባለው።
የአቅም ግንባታ የውይይት መድረኩ እስከታችኛው የፓርቲ መዋቅር ድረስ እንደሚወርድ ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!