ዘላቂ ሠላም ለማረጋገጥ የበኩላችንን አስተዋጽኦ ማበርከት ይኖርብናል -የሃይማኖት አባቶች
አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአብሮነትና የመከባበር እሴቶቻችንን ለወጣቶች በማስረጽ ወጣቱ ኃይል የሠላም ዘብ እንዲሆን የበኩላችንን አስተዋጽኦ ማበርከት ይኖርብናል ሲሉ የሃይማኖት አባቶች ገለጹ፡፡
የሠላም ሚኒስቴር” ማኅበራዊ ሐብቶቻችን ለዘላቂ ሠላማችን” በሚል መሪ ሃሳብ ከሃይማኖት አባቶች ጋር ሀገራዊ የምከክር መድረክ አካሄዷል፡፡
ህዝብና መንግስትን ለማጋጨት የሃይማኖት ጭምብል ለብሰው የሀገርን ሠላም እያደፈረሱ ያሉ አካላት አሉ ያሉት በመድረኩ የተሳተፉ የሃይማኖት አባቶች፥ በእነዚህ አካላት ላይ መንግስት ህጋዊ እርምጃ ሊወስድ ይገባል ብለዋል፡፡
ወጣቱ ትውልድ የመከባበር እና የመቻቻል ባሕልን እንዲያዳብር በማስተማር እና በመገሰጽ ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ እኛ የሃይማኖት አባቶች ከፍተኛ ሃላፊነት አለብን ነው ያሉት፡፡
የምክከር መደረኩን በይፋ ያስጀመሩት በሠላም ሚኒስቴር የሠላም ግንባታና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ታዬ ደንደአ በበኩላቸው ÷ ሠላም ለሁሉም ነገር መሠረት ነው ፤ ስለሆነም ዘላቂ የሆነ ሠላምን ለማረጋገጥና ሠላምን ለማስረፅ የሃይማኖት አባቶች ትልቅ ሚና አላቸው ብለዋል፡፡
ሚኒስትር ድኤታው ከዚህ ቀደም የነበረውን ኢትዮጵያዊ ጥንካሬ ለማስቀጠል የሃይማኖት አባቶች በየቤተ-እምነቱ የሚሰጠውን ትክክለኛ ሃይማኖታዊ አስተምህሮ ሊያጠናክሩ እንደሚገባ መናገራቸውን ከሰላም ሚኒስቴር ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!