Fana: At a Speed of Life!

19ኛውን ሀገር አቀፍ የባህል ስፖርቶች ሻምፒዮና ውድድር እና 15ኛው የባህል ፌስቲቫልን ለማስተናገድ ዝግጅት ተጠነቀቀ

• ውድድሩ በደብረ ብርሀን ከተማ ከየካቲት 6 እስከ 13 ይካሄዳል
አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 19ኛውን ሀገር አቀፍ የባህል ስፖርቶች ሻምፒዮና ውድድር እና 15ኛው የባህል ፌስቲቫልን ለማስተናገድ ዝግጅት መጠናቀቁን የሰሜን ሸዋ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ አስታወቀ፡፡
የመምሪያው ሃላፊ አቶ ብርሀን ጨርቆስ ዛሬ በሰጡት መግለጫ÷ ለባህል ስፖርቶች ሻምፒዮና የሚመጥን የውጭ እና የውስጥ የሜዳ ዝግጅት ተከናውኗል ብለዋል፡፡
የባህል ስፖርቱ ሰፊ የሜዳ ሽፋን የሚያስፈልገው እና በጥንቃቄ የሚሰራ ስለሆነ ለዝግጅቱ የሚመጥን የመወዳደሪያ ሜዳዎች በሚፈለገው የጥራት ልክ ተዘጋጅተው እና መሰረተ ልማቶች ተሟልቶላቸው ውድድሩን ለማስተናገድ ተዘጋጅተዋል ብለዋል።
በደብረ ብርሀን ከተማ ከየካቲት 6 እስከ 13 ቀን 2014 ዓ.ም የሚካሄደው 19ኛው ሀገር አቀፍ የባህል ስፖርቶች ሻምፒዮና ውድድር እና 15ኛው የባህል ፌስቲቫል በተሳካ ሁኔታ ለማስተናገድ ማህበረሰቡ የእንግዳ ተቀባይነት ባህሉን እንዲያሰመሰክር ጥሪ አቅርበዋል።
በባህል እስፖርቱ እና ፌስቲቫሉ ላይ ከሁሉም ክልሎች ከ1ሺህ በላይ ሰዎች ተሳታፊ ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በኤልያስ ሹምዬ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.