Fana: At a Speed of Life!

40ኛው የአፍሪካ ህብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ጉባኤ ዛሬም ቀጥሎ በመካሄድ ላይ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 40ኛው የአፍሪካ ህብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ጉባኤ ዛሬም ቀጥሎ በአህጉሪቱ በሽታዎችን መከላከል እና መቆጣጠር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መምከሩን አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናገሩ፡፡
በህብረቱ አባል አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ደረጃ እየተካሄደ ከሚገኘው የስራ አስፈጻሚዎች ጉባኤ ጎን ለጎን የሁለትዮሽ ውይይቶች እየተከናወኑ እንደሚገኙም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ለጋዜጠኞች ገልጸዋል፡፡
የህብረቱ ስራ አስፈጻሚዎች የአፍሪካ በሽታ መከላከል እና መቆጣጠር ማዕከል ያለበትን ደረጃ የመከሩ መሆናቸውን ገልጸው÷ አፍሪካ አስተማማኝ በጀት ኖሯት የጤና ዘርፉን የግድ ማዘመን ይገባታል መባሉን ጠቁመዋል፡፡
ምክር ቤቱ በቀሪ የውይይት ጊዜው የፊታችን ቅዳሜ እና እሁድ በሚካሔደው 35ኛው የሕብረቱ የመሪዎች ጉባኤ ላይ በሚቀርቡ ረቂቅ አጀንዳዎች ላይም እንደሚመክር ንው አምባሳደር ዲና የገለጹት፡፡
ከስራ አስፈጻሚ ምክር ቤቱ ጉባኤ ጎን ለጎን በተደረጉ የሁለትዮሽ ምክክሮች ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከሞሮኮ፥ ቱኒዚያና ኮሞሮስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር መወያየታቸውንም ተናግረዋል፡፡
በበርናባስ ተስፋዬ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.