Fana: At a Speed of Life!

የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር እዮብ ተካልኝ ከኬንያ ኢነርጂ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር እዮብ ተካልኝ ከኬንያ የኢነርጂ ሚኒስትር አምባሳደር ሞኒካ ጁማ ጋር ተወያይተዋል፡፡
 
በውይይታቸውም በሁለቱ አገራት የሃይል አቅርቦት ትብብር ላይ ፍሬያማ ውይይት ማድረጋቸውን ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
ኢትዮጵያ ለሶስት ጎረቤት አገራት ማለትም ለኬንያ፣ ለሱዳን እና ጅቡቲ በድምሩ 1 ነጥብ 6 ቢሊየን ኪሎ ዋት የኤሌክትሪክ ሃይልን እንደምትሸጥ ማስታወቋ ይታወሳል፡፡
 
በዚህ መሰረትም እስካሁን የኢነርጂ ኤክስፖርት ወዳልተጀመረበት ኬኒያ ወደ 695 ኪሎ ዋት ሰዓት የኤሌክትሪክ ኃይል ለማቅረብና 48 ነጥብ 65 ሚሊየን ዶላር ለማግኘት ዕቅድ መያዙን መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.