Fana: At a Speed of Life!

በአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ በአህጉሪቱ የኮቪድ -19 ክትባት ማምረቻ ሊገነባ እንደሚገባ ተመክሯል-አምባሳደር ዲና ሙፍቲ

አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ በአህጉሪቱ የኮቪድ -19 ክትባት ማምረቻ ሊገነባ እንደሚገባ መመከሩን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናግረዋል።
 
ቃል አቀባዩ ዛሬ ጠዋት በሰጡት መግለጫ ÷ 35ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ በሰላም እና ጸጥታ፣ በኮቪድ -19 እና በአፍሪካ ልማት ባንክ ሪፖርት ላይ መወያየቱን ጠቅሰዋል፡፡
 
የኮሮና ቫይረስ በአህጉሪቱ መጠነ ሰፊ የሆነ ጉዳት እያስከተለ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን ÷ ቫይረሱ እያደረሰ ያለውን መጠነ ሰፊ ጉዳት ለመቀነስ አፍሪካ ክትባት ልታመርት ይገባታል ነው የተባለው።
 
በመሆኑም ሀገራት ክትባት ለማምረት የሚያስችል እንቅስቃሴ መጀመር እንዳለባቸው ነው የተጠቆመው ።
 
በሌላ በኩል ኅብረቱ በሰላም እና ጸጥታ ጉዳይ ላይ የመከረ ሲሆን÷ በጉዳዩ ላይ በኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የቀረበውን ሪፖርትም አድምጧል።
 
በሪፖርቱም በአፍሪካ ህገ መንግስታዊ ያልሆነ የመንግስት ለውጥን ለመከላከል ልዩ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ተመላክቷል።
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.