ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ከኬንያና ከሴኔጋል ፕሬዚዳንቶች ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከ35ኛው የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ ጎን ለጎን ከኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታና ከሴኔጋሉ ፕሬዚዳንትና የህብረቱ የወቅቱ ሊቀመንበር ማኪ ሳል ጋር በሁለትዮሽና በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።
በውይይታቸው ኢትዮጵያ ሰላምን ለማረጋገጥ እያከናወነቻቸው ያሉ ተግባራት ላይ መክረዋል፡፡

ውይይቱን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው÷ በጋራ ጉዳዮች ላይ ትብብርን ለማጠናከር ያለን ቁርጠኝነት የፀና ነው ብለዋል፡፡