አምባሳደር ሙሉ ሠሎሞን አዲሱ የጀርመን መንግሥት ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ግንኙነት እንዲያጠናክር ጠየቁ
አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ ) በጀርመን የኢፌዴሪ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ሙሉ ሰሎሞን አዲሱ የጀርመን መንግሥት ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ግንኙነት እንዲያጠናክር ጠየቁ፡፡
አምባሳደሯ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የአፍሪካና የሣህል ዳሬክተር ከሆኑት አምባሳደር ሮበርት ዶልገር ጋር ውይይት አድርገዋል።
አምባሳደር ሙሉ፥ የጀርመን መንግሥት ላለፉት ሶስት ዓመታት ለሰጠው የተለያዩ ድጋፎች ምስጋናቸውን ገልጸው፣ አዲሱ የጀርመን መንግሥት በሁለቱ ሀገራት መካከል በተለያዩ መስኮችን ያለውን ትብብርን ከወትሮው በበለጠ እንዲያጠናከር ነው የጠየቁት።
የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተም አሸባሪው የህወሃት ቡድን በአማራና በአፋር የሚያደረገውን ትንኮሳና በንፁሃን ሠላማዊ ሰዎች የሚያደርገውን ጭፍጨፋ እንዲሁም መተላለፊያ ኮሪደሮችን በመዝጋት ለትግራይ ህዝብ ሰብዓዊ እርዳታ እንዳይገባ ማገዱን በይፋ እንዲያወግዝ አምባሳደር ሙሉ ጠይቀዋል።
አሸባሪውን ህወሃት በወረራ ከገባበት የአማራና የአፋር ክልሎች መንግሥት ካስወጣው በኃላ በሰሜኑ ክፍል አንጻራዊ ሠላም መኖሩን ገልጸው፣ ”በኢትዮጵያ ሠላም የለም፣ ከሀገር ውጡ ” በማለት በሀገራችን ላይ የተሠነዘረው የሀሰት ዜና፣ አደገኛና አፍራሽ የወሬ ዘመቻ በመላው ሕዝባችን ርብርብና አንድነት አስረድተዋል።
በኢትዮጵያ ሠላም ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካ ቀንድ ሠላም ያለውን ፋይዳ እንዲረዱ፣ ጀርመን በአውሮፓ ህብረትም ውስጥ ባላት የተጽዕኖ ፈጣሪነት ሚናዋ ሃላፊነቷን እንድትወጣ፣ ህወሃት ላደናቀፈው የሰብአዊ አርዳታአቅርቦት፣ የኢትዮጵያን መንግስት ያለአግባብ መውቀስና መጫን መቆም እንዳለበት አሳስበው፥ የጀርመን መንግስት ተገቢውን ድጋፍ ለኢትዮጵያ አንዲሰጥ መጠየቃቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!