Fana: At a Speed of Life!

19ኛው የኢትዮጵያ ባሕል ስፖርቶች ውድድር በደብረ ብርሃን ከተማ አስተናጋጅነት ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣የካቲት 1፣2014 (ኤፍ ቢሲ) 19ኛው የኢትዮጵያ ባሕል ስፖርቶች ውድድርና 15ኛው የባሕል ፌስቲቫል በደብረ ብርሃን ከተማ አስተናጋጅነት እንደሚካሄዱ የኢትዮጵያ ባህል ስፖርቶች ፌዴሬሽን አስታወቀ።
ውድድሩ ከየካቲት 6 እሰከ 13 ድረስ ሲካሄድ በ10 የስፖርት አይነቶች ከትግራይ ክልል ውጭ አዲሱን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ጨምሮ ከተማ አስተዳዳሮች የተወጣጡ ከ900 በላይ ስፖርተኞች እንደሚካፈሉበት ፌደሬሽኑ ዛሬ በሰጣዉ መግለጫ አስታውቋል ፡፡
የኢትዮጵያ ባሕል ስፖርቶች ፌዴሬሽን ጽሕፈት ቤት ሃላፊ አቶ በላይነህ ኃይሌ ውድድሩን በተሳካ ሁኔታ ለማካሄድ አስፈላጊ ቅድመ ዝግጅት ተደርጓል ብለዋል።
ከአዘጋጁ አማራ ክልል ጋር በቅንጅት አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት መደረጉንም ነው ሃላፊው የተናገሩት።
በሃገር አቀፍ ደረጃ ህግ እና ስርዓት ያልወጣላቸው ከ293 የባህል ስፖርቶች ሲኖሩ በቀጣይ ጥናት ተደርጎባቸው ወደ ውድድር እንደሚገቡ ተገልጿል ፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.