የብራዚል ኩባንያዎች በኢትዮጵያ የኢነርጂ ልማት ዘርፍ ለመሰማራት ፍላጎት እንዳላቸው ተገለፀ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 10 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የብራዚል ኩባንያዎች በኢትዮጵያ የኢነርጂ ልማት ዘርፍ መሰማራት እንደሚፈልጉ የሀገሪቱ አምባሳደር ገለጹ።
የውሃና ኢነርጂ ሚንስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ሃብታሙ ኢተፋና ሌሎች የሚኒስቴሩ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች በኢትዮጵያ የብራዚል አምባሳደር ሉዊዝ ኤድዋርዶ እና ከባልደረቦቻቸው ጋር ተወያይተዋል ።
በውይይቱ በኢነርጂ በተለይ የሶላር የሃይል አማራጭን ለማልማት፣ በንጹህ መጠጥ ውሃ ፍሎራይድን ጨምሮ የተበከለ ውሃን ማከሚያ ቴክኖሎጂዎችን በተመለከተ በጋራ ለመስራት መክረዋል።
በተጨማሪም ብራዚል የእንቦጭ አረምን በማስወገድ ረገድ ያለውን ጥሩ ተሞክሮና ቴክኖሎጂ ለመጋራት ተወያይተዋል።
ሚኒስቴሩ እና ኤምባሲው በቅርበት ስራዎችን ለመስራት እንዲያስችላቸውም ተወካይ መድበው ለመስራት መስማማታቸውን ከውሃና ኢነርጂ ሚንስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!