በጋምቤላ ክልል የእንቦጭ አረም የማስወገድ መርሃ ግብር ተጀመረ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ክልል በታታ ሀይቅ ላይ የተከሰተውን እንቦጭ አረም የማስወገድ መርሃ ግብር የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ተጀምሯል።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ተወካይ አቶ ጁል ናንጋል፥ አረሙ በዓሳ ሀብት ላይ ከፍተኛ ችግር የሚፈጥር መሆኑን አመልክተው አረሙ በበለጠ ከመስፋፋቱ በፊት መላው የክልሉ ህዝብና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ለመከላከል ጥረት እንዲያደረጉ አሳስበዋል።
የክልሉ መንግስት አረሙን ለመከላከል ለሚደረገው ጥረት አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ ለመስጠት ዝግጁ መሆኑም ገልፀዋል።
የክልሉ አካባቢ ደንና አየር ንብረት ለውጥ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ኮማንደር ኡማን ኡጋላ በበኩላቸው÷ ቀደም ሲል የታታ ሀይቅ ስፋት 457.58 ሄክታር የነበረ መሆኑን ጠቁመው በጉዳት ምክንያት አሁን የቀረው የውሃ አካል 251.86 ሄክታር ብቻ መሆኑን አመልክተዋል።
የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ኡጁሉ ኡኮክ ÷ ዩኒቨርስቲው አረሙን ለማጥፋት የሚደረገውን ጥረት እንደሚያግዝ አስረድተው በሰው ሀይልና በምርምር የተደገፈ ምላሽ ለመስጠት መዘጋጀታቸውን መናገራቸውን ከጋምቤላ ክልል ፕሬስ ሴክሬታሪያት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!