124ኛውን የአድዋ ድል በዓል ለመዘከር የተለያዩ ህብረተሰብ ክፍሎች የሚሳተፉበት የአድዋ ጉዞ ተጀመረ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 17፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር 124 ኛውን የአድዋ ድል በዓል ለመዘከር ያዘጋጀው የአድዋ ጉዞ በዛሬው ዕለት ተጀምሯል።
በመነሻ ዝግጅቱ ላይ የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳውን ጨምሮ የተለያዩ የመንግሰት የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።
ጉዞው “አድዋ የአንድነታችን ድርና ማግ” በሚል መሪ ቃል ነው እየተካሄደ የሚገኘው።
መነሻውን አዲስ አበባ አድዋ ድልድይ ላይ ያደረገው ይህ ጉዞ ሰንዳፋ፣ አንጎላላ፣ ወረ ኢሉ፣ ውጫሌ፣ ማይጨው፣ እንዳ ኢየሱስ እና ሌሎች ታሪካዊ ቦታዎችን በመጎብኘት መዳረሻውን የአድዋ ተራራ ላይ የሚያደርግ ይሆናል።
ጉዞው 124ኛውን የአድዋ ድል ከመዘከር ባለፈ በማህበረሰቡ ዘንድ ግንዛቤ ለመፍጠር ያለመ መሆኑን ዶክተር ሂሩት ካሳው ተናግረዋል።
በጉዞ መርሃ ግብሩ ላይ የክልል ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ሀላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች እና የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል።
በዘመን በየነ