Fana: At a Speed of Life!

የአሜሪካ የመጀመሪያዋ ሴት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማዲሊን ኦልብራይት ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካ የመጀመሪያዋ ሴት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማዲሊን ኦልብራይት በ84 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

ማዲሊን ኦልብራይት በፕሬዚዳንት ቢል ክሊንተን የስልጣን ዘመን በውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ያገለገሉ በዓለም ዙሪያ የሚታወቁ ዲፕልማት ነበሩ።

ኦልብራይት በአውሮፓውያኑ የቀን አቆጣጠር በ1937 በቺኮዝላቫኪያ፣ፕራግ ነበር የተወለዱት።

የዲፕሎማት ልጅ የነበሩት አልብራይት ከቤተሰባቸው ጋር ወደ ዩናይትድ ስቴትስ የተሰደዱ ሲሆን፥ በፈረንጆቹ 1957 ላይ ነበር የአሜሪካ ዜግነት ያገኙት።

በጂሚ ካርተር የስልጣን ዘመን ወደ ዋይት ሃውስ ገበትው ያገለገሉት ዲፕሎማቷ፥  በክሊንተን የስልጣን ዘመን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነታቸው አስቀድመው በተመድ የአሜሪካ አምባሳደር በመሆን አገግለዋል።

 

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.