Fana: At a Speed of Life!

በጨው ምርት ግብይት እና የምርት ሂደቱ በዜጎች ጤና ላይ ባለው ተጽዕኖ ዙሪያ በተደረገ ጥናት ላይ ውይይት ተደረገ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕድን ሚኒስቴር፣ የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር እና የአፋር ክልል በጨው ምርት እና ግብይት ላይ እንዲሁም የምርት ሂደቱ በዜጎች ጤና ላይ ባለው ተጽዕኖ ዙሪያ በተደረገ ጥናት ላይ ተወያይተዋል፡፡

የማዕድን ሚኒስትር ኢንጅነር ታከለ ኡማ በማህበራዊ ትስስት ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ ÷ የጨው ምርትና ግብይት ላይ ያተኮረ እንዲሁም የምርት ሂደቱ በዜጎች ጤና ላይ ባለው ተጽዕኖ ዙሪያ የንግድ ሚኒስቴር፣ ጤና ሚኒስቴር እና የማዕድን ሚኒስቴር ባለሙያዎች በትብብር ጥናት አድርገዋል፡፡

በተካሄደው ጥናትም ባለሙያዎች በርካታ ግብዓቶችን እና ግኝቶችን መለየታቸውን ነው የገለጹት፡፡

በጥናቱ ዙሪያም ኢንጂነር ታከለ ኡማ እና የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር አቶ ገብረመስቀል ጫላ ከአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ እና ሌሎች የክልሉ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በጉዳዩ ላይ በዛሬው ዕለት በሰመራ መክረዋል፡፡

በውይይታቸውም በጥናቱ ሙሉ አውድ ላይ መግባባት መፍጠር መቻሉን ኢንጂነር ታከለ ኡማ ተናግረዋል፡፡

በጥናት የተለየው ግኝትም በቅርቡ በተለያዩ አካላት ሃሳብ ከተሰጠበት በኋላ ውሳኔው ይፋ የሚደረግ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.