የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እና የተመጣጠነ አመጋገብን እውን ለማድረግ የጓሮ አትክልት ሥፍራዎች እንዲኖሩ ማድረግ የከተማ ግብርናን ለማጠናከር ወሳኝ ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ
አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 27 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እና የተመጣጠነ አመጋገብን እውን ለማድረግ በቤት ውስጥ የጓሮ አትክልት ሥፍራዎች እንዲኖሩ ማድረግ የከተማ ግብርናን ለማጠናከር ወሳኝ መሆኑን አስታወቁ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፥ የጓሯችን ስፋት ምንም ያህል ትንሽ ቢሆን ወይም ጓሮ ባይኖረን እንኳ፣ ከተሞቻችን ዕድገታቸውን ሲቀጥሉ፣ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እና የተመጣጠነ አመጋገብን እውን ለማድረግ በቤት ውስጥ የጓሮ አትክልት ሥፍራዎች እንዲኖሩ ማድረግ የከተማ ግብርናን ለማጠናከር ወሳኝ ነው ብለዋል።
በተደጋጋሚ ጥቅም ላይ በሚውሉ ቁሳቁሶች አማካኝነት ወደላይ የሚዘረጉ የአትክልት ቦታዎችን መሥራት ለብዙኃኑ ቀላል መሆኑንም አውስተዋል።
ቤተሰቦች ይህንን የማድረግ ዐቅማቸውን እንዲፈትሹና እንዲጠቀሙበት አበረታታለሁ ሲሉም ጠቅላይ ሚኒስትሩ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!