Fana: At a Speed of Life!

የአቶ ውብሸት ወርቃለማሁ የቀብር ስነ ስርዓት ተፈፀመ

 አዲስ አበባ፣ የካቲት 25፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአንጋፋው የማስታወቂያ ባለሙያ አቶ ውብሸት ወርቃለማሁ የቀብር ስነ ስርዓት ተፈፀመ።
የቀብር ስነ ስርዓቱ ቤተሰቦቻቸው፣ ወዳጅ ዘመድ፣ የስራ አጋሮቻቸው እና አድናቂዎቻቸው በተገኙበት ዛሬ 9 ሰዓት በመንበረ ፀባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተ ክርስቲያን ተፈፅሟል።
አቶ ወብሸት ባደረባቸው ህመም በቅዱስ ገብርኤል ሆስፒታል በህክምና ሲረዱ ቆይተው ባሳለፍነው ቅዳሜ ነበር ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት።
በኢትዮጵያ የማስታወቂያ ኢንዱስትሪ ውስጥ ፈር ቀዳጅ የነበሩት አቶ ውብሸት፥ በሃገር ፍቅር ቴአትር ቤት ቴአትሮችን እንዲሁም የቴሌቪዥን ድራማዎችን በመፃፍ እና በመተወን የጥበብ ጎራውን መቀላቀላቸው ይነገራል።
መቀጠልም አንበሳ የተባለ የማስታወቂያ ድርጅት በመክፈት በዘርፉ ሲሰሩ ቆይተዋል።
በተጨማሪም አቶ ውብሸት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የኢትዮጵያ የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ቡድን አባል በመሆን ሀገራቸውን በመወከል የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን በማሻሻሉ ረገድ የድርሻቸውን ተወጥተዋል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.