Fana: At a Speed of Life!

የሕንድ ባለሃብቶች ኢትዮጵያ ቅድሚያ በምትሰጣቸው የኢንቨስትመንት አማራጮች ለመሳተፍ ፍላጎት እንዳላቸው ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የመካከለኛው ምሥራቅ፣ የእስያና ፓስፊክ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራል አምባሳደር ዶ/ር ገበየሁ ጋንጋ ከሕንድ የቢዝነስ ልዑካን ቡድን ጋር ተወያይተዋል፡፡
የልዑካን ቡድን አባላቱ በሕንድ ኢኮኖሚ ንግድ ድርጅት አስተባባሪነት በኢትዮጵያ የቅድመ-ኢንቨስትመንት ጉብኝት እያደረጉ ነው፡፡
የሕንድ ኢኮኖሚ ንግድ ድርጅት ሊቀመንበር ዶ/ር አሲፍ ኢቅባል÷ድርጅታቸው የሕንድ ኩባንያዎች በውጪ አገራት የንግድና ኢንቨስትመንት ተሳትፏቸውን ማሳደግ እንዲችሉ የማስተባበርና የማገዝ ሥራ እንደሚሠራ ተናግረዋል፡፡
በአትዮጵያ ያሉ የኢንቨስትመንት አማራጮችን ለማጥናት የጉብኝቱን መርሐ ግብር ማዘጋጀታቸውን ነው የገለጹት፡፡
በልዑካን ቡድኑ የተካተቱ ኩባንያዎች በግብርና፣ በግብርና ማቀነባበሪያ፣በጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ምርት፣ በማዕድን፣ በጤና፣ በትምህርት እና በኢንፎረሜሽን ቴክኖሎጂ ዘርፎች የተሠማሩ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡
ኩባንያዎቹ በእነዚህ ዘርፎች በኢትዮጵያ ለመሰማራት ፍላጎት እንዳላቸው አስረድተው÷ ደርጅታቸው በዚሁ ረገድ ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን እና ከሚመለከታቸው የኢትዮጵያ ተቋማት ጋር በትትብር ለመሥራት ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ልዑካን ብድኑ ቡልቡላ የተቀናጀ የአግሮ ኢንዱስትሪ፣ ቂሊንጦ እና ቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርኮችን በመጎብኝትና ከሥራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት በማድረግ ፓርኮቹ በተለይም በግብርና ማቀነባበሪያ እና በጨርቃጨርቅ ኢንቨስትመንት ዘርፎች መሰማራት የሚፈልጉ ባለሀብቶችን በማስተናገድ ረገድ ያላቸውን አቅምና ምቹ ሁኔታዎች አስመልክቶ ጠቃሚ መረጃዎች መግኘት መቻላቸውን አብራርተዋል፡፡
በቀጣይ ድርጅታቸው ከተለያዩ በሕንድ እና በኢትዮጵያ ከሚገኙ ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር እና አቅም ያላቸውን ኩባንያዎች በማስተባበር በአፍሪካ ደረጃ በአዲስ አበባ ትልቅ የቢዝነስ ኮንፈርንስ ለማዘጋጀት ማቀዳቸውን ጠቁመዋል፡፡
አምባሳደር ዶ/ር ገበየሁ ጋንጋ በበኩላቸው÷በኢትዮጵያ እና በህንድ መካከል ያለው ዘርፈ-ብዙ ትብብር የሁለቱን ሀገሮች የግሉ ዘርፍ ትስስርን በማጣናከር እንዲሁም የህንድ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ከማስቻል አኳያ ምቹ ሁኔታን የሚፈጥር መሆኑን አንስተዋል፡፡
የልዑካን ቡድን አባላት ኢትዮጵያ ቅድሚያ በትሰጠው የኢንቨስትመንት ዘርፎች ለመሠማራት ላሳዩት ፍላጎት ማመስገናቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
የልዑካን ብድኑ አባላት በኢትዮጵያ ያለውን ሰፊና ምቹ የኢንቨስትመንት አማራጮች እና የገበያ ዕድሎችን በመጠቀም መዋዕለነዋያቸውን በማፍስሰ ወደ ተጨባጭ ተግባራ እንዲሸጋገሩ አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚደረግ ገልጸዋል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.