ለጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከ32 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ የህክምና ግብዓቶች ድጋፍ ተደረገ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ1፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከ32 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጣ የህክምና ግብዓት እና አልሚ ምግብ ድጋፍ ተደረገለት፡፡
ድጋፉን ምህረት የህክምና አቅርቦት ቡድን እና የክርስቲያን ኤይድ ድርጅት ከጄ ኤም ዩ ዩኒቨርሲቲ እና ከሄኖክ አራጋው ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር ያደረጉት መሆኑ ተገልጿል፡፡
ድርጅቱ በሆስፒታሎች በከፍተኛ ደረጃ የህክምና ግብዓት እጥረት መኖሩን በመረዳት አሜሪካ ከሚኖሩ ግብረ-ሰናይ ድርጅቶች ጋር በመተባበር ከአሁን በፊት በጦርነቱ ለተጎዱ አካባቢዎች በአራት ዙር 3 ነጥብ 6 ሚሊየን ዶላር የሚያወጡ የተለያዩ የህክምና ግብዓቶች ድጋፍ ማድረጉ ተመላክቷል፡፡
በቀጣይም ለአርሶአደሮች የንፁህ መጠጥ ውሃ የማቅረብ እና በማር ምርት ላይ የተሰማሩ አርሶ አደሮችን ለመደገፍ ፕሮጀክቶችን ቀርጾ ተግባራዊ ለማድረግ እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑን የድርጅቱ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር ጥላሁን መኮንን ተናግረዋል፡፡
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር እሰይ ከበደ በበኩላቸው ÷ ከምህረት የህክምና አቅርቦት ቡድን ጋር የመግባቢያ ሰነድ ከተፈራረሙ አንድ ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በጤናው ዘርፍ ለሚታዩ ጉልህ የመድሃኒት እና የቁሳቁስ ችግሮች በመሸፈን ከፍተኛ ስራ መስራቱን ተናግረዋል፡፡
ድርጅቱ የተለያዩ የህክምና መሳሪያዎችን እና መድሃኒቶችን ከውጪ ሀገር ወደ ኢትዮጵያ ማድረስ መሆኑን ገልጸው÷የተጠቃሚዎችን ልየታ እና የማጓጓዝ ስራዎችን የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ እየሰራ እንደሆነ መጠቆማቸውን ከዩኒቨርሲቲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!