Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ በመዲናዋ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በአዲስ አበባ እየተከናወኑ የሚገኙ ሰው ተኮር የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል።
 
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባስቀመጡት አቅጣጫ መሠረት የተጀመሩት በ1ወር ከ20 ቀናት የሚከናወኑ ሰው ተኮር የተቀናጁ የልማት ሥራዎች በአምስት ክፍለ ከተሞች እየተከናወኑ እንደሚገኙ ተመላክቷል፡፡
 
በአምስት ክፍለ ከተሞች የተጀመሩት የልማት ሥራዎች ሞዴል ክፍለ ከተሞችን የመፍጠር ፕሮጀክት መሆኑ ተገልጿል፡፡
 
ጉብኝቱ የአዲስ አበባ አስተዳደር አስተባባሪ ኮሚቴ እና የካቢኔ አባላት በተገኙበት የተካሄደ መሆኑንም ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.