Fana: At a Speed of Life!

የጋሞ አባቶችን የሰላም ተምሳሌትነት የሚዘክር የባህል ሲምፖዚየም ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የጋሞ አባቶችን የሰላም ተምሳሌትነት የሚዘክር የባህል ሲምፖዚየም በዛሬው እለት ተካሄደ።

ሲምፖዚየሙ “የጋሞ አባቶች የሰላም ተምሳሌትነት ለሃገር ግንባታ” በሚል መሪ ቃል በሚሊኒየም አዳራሽ ተካሄዷል።

የጋሞ ልማት ማህበር አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ባዘጋጀው ሲምፖዚየም በእርጥብ ሳራቸው እሳትን በማጥፋት ፍቅርን የሰበኩ የጋሞ አባቶች ዘመን ተሻጋሪ የግጭት አፈታት ጥበባቸው ተዘክሯል።

በአዲስ አበባ ለመጀመሪያ ጊዜ በተዘጋጀው ሲምፖዚየም ላይ የጋሞ ተወላጆች፣ ወዳጆች እና የልማቱ ደጋፊዎችን ጨምሮ 30 ሺህ የሚገመቱ ታዳሚዎች ተሳትፈዋል።

በሲምፖዚየሙ ላይ የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፊሪያት ካሚል ፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማን ጨምሮ የክልል መንግስታት ከፍተኛ የሥራ ሀላፊዎች፣ መቀመጫቸውን በአዲስ አበባ ያደረጉ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች፣ ዲፕሎማቶች፣ ታዋቂ ግለሰቦች እና ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በመርሃ ግብሩ የጋሞ ባህላዊ ምግቦች እና የኪነጥበብ ሥራዎች መቅረባቸውን ከጋሞ ዞን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.