ስዊድን እና ፊንላንድ ኔቶን ቢቀላቀሉ ሩሲያን አያሰጋትም – ቭላድሜር ፑቲን
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ስዊድን እና ፊንላንድ የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅትን (ኔቶ) ቢቀላቀሉ በሩሲያ ላይ የሚፈጥሩት ምንም ዓይነት ሥጋት እንደማይኖር የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሜር ፑቲን ገለጹ፡፡
ፕሬዚዳንት ፑቲን ይህን ያሉት ሞስኮ ለሚገኘው የጋራ ደኅንነት ሥምምነት ድርጅት አባል ሀገራት መሪዎች መሆኑ ተመላክቷል
ነገር ግን ኔቶ ወታደራዊ መሠረተ ልማቱን በቀጠናው በተለየ መልኩ ካጠናከረ እና ለሩሲያ ሥጋት የሚፈጥር ከሆነ አጸፋዊ ምላሽ እንደሚሰጡ አስጠንቅቀዋል።
ቀደም ሲል የሩሲያ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ሪያብኮቭ እና የሀገሪቱ በርካታ ዲፕሎማት ÷ ፊንላንድ እና ስዊድን ኔቶን ለመቀላቀል ያቀረቡት ጥያቄ ከባድ መዘዝ እንደሚያስከትል እና እንደማይቀበሉት ማስጠንቀቃቸው ይታወሳል፡፡
በዛሬው ዕለትም አሜሪካ ሀገራቱ ኔቶን እንዲቀላቀሉ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤቷ በኩል በ18 የሪፐብሊካን ተቃውሞ በአብላጫ ድምጽ መደገፏን ዘ ሂልን ጠቅሶ ሲጂቲኤን ዘግቧል።