አቶ ሙስጠፌ በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ድል ላስመዘገቡ አትሌቶች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሙስጠፌ መሀመድ በ18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ድል ላስመዘገቡ አትሌቶች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ርዕሰ መስተዳደሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ ጀግኖች አትሌቶቻችን እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡
ርዕሰ መስተዳደሩ በተለይም የአትሌቲክስ ቡድኑን ሙያዊ እና ብቃት ባለው ሁኔታ በመምራት አመረቂ ውጤት ላስመዘገበችው ለፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ኮሎኔል ደራርቱ ቱሉ የላቀ ምስጋና አቅርበዋል፡፡